በሰሜን ጎንደር ዞን ለሚሊሻ አባላት ወታደራዊ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

52

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ለሚገኙ ነባርና አዳዲስ የሚሊሻ አባላት በዞኑ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ወታደራዊ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

በሥልጠናው ማስጀመሪያ የተገኙት ጀኔራል አማረ ገብሩ የሚሊሻውን ወታደራዊ አቅም በመገንባት በዞኑ የሚንቀሳቀሰውን ጽንፈኛው ኀይል አከርካሪውን ለመምታት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል።

ጽንፈኛው ኀይል በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በመቅረፍ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ያስችላል ብለዋል። አረጋግጦ የተለያዩ የሥራ ዘርፎችን ማንቀሳቀስ እንዳይችል እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ዝግ እንዲሆኑና ተማሪዎች ካላስፈላጊ ቦታዎች እንዲውሉ ምክንያት መሆኑን ገልፀው

የሥልጠናው ዋና አላማ የጸጥታ አባላትን ወደ አንድ መስመር ለማምጣትና እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አሁን ያለውን አንጻራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሥልጠናው ትልቅ አቅም ይሆናል ሲሉ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ተወካይ ሙላት እሸቴ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የአማራ ክልል ግብርና ጥራትና ደህንነት ባለሥልጣን አማካሪ ጥላሁን ዓለምነህ እንደገለጹት ይህ ኀይል የሕዝቡን እና የሀገሩን ሰላም ለማስጠበቅ ሲል መስዋእትነትን እየከፈለ ያለ መሆኑን ገልፀው ሥልጠናው በቀጣይ ለሚሰጡት ተልእኮች በብቃት እንዲፈጽም ያስችለዋል ብለዋል።

ሥልጠናው ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚሰጥ የደባርቅ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረ ብረሃን ከተማ አሥተዳደር አንደኛ ደረጃ የገበያ ማዕከል ሊገነባ ነው።
Next articleበአንጎለላ እና ጠራ ወረዳ ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ ሚሊሻዎች ተመረቁ።