
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምስራቅ ጎጃም ዞን በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አሥተዳደሮች የሰላም አሰከባሪና የሚሊሻ አባላትን አሠልጥኖ እያስመረቀ ነዉ።
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአዋበል ወረዳ ለተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩ አዲስና ነባር የሰላም አሰከባሪና የሚሊሻ አባላት ሥልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል።
የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰላም ለማስጠበቅ ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩት የሰላም አስከባሪና የሚሊሻ አባላት ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን በቁርጠኝነት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!