
ደብረ ማርቆስ፡ ታኅሳስ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ተቋማት ባላቸው የሥነ-ምግባር መርሆዎች እና ሊገነቡት ባስቀመጡት እሴት መሰረት ተገቢ አገልግሎት በመስጠት ብልሹ አሠራርን ለመቀነስ ሊሠሩ ይገባል ሲሉ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትሕ መምሪያ ኀላፊ አበበ አወቀ ገለልጸዋል።
ወጣቶች ዛሬን የሚገነቡ እና ነገን የሚረከቡ በመሆናቸው በመልካም ሰብዕና እንዲገነቡ በጋራ መሥራት አስፈላጊ ነው ተብሏል።
ለዜጎች ፍትሐዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ተቋማት የአሠራር ግልፀኝነት እና ተጠያቂነትን በመዘርጋት የብልሹ አሰራር አባባሽ ምክንያቶችን ለይቶ መፍታት ይገባል ያሉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ዋለ አባተ “ነገን በሰብዕና ለመገንባት ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል ማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል ።
ለማኅበረሰቡ ግልፅና ተዓማኒነት ያለው አገልግሎት በመስጠት በአሠራራቸው የሕዝብንና የሀገር አደራን ለመወጣት እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት የምስራቅ ጎጃም ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ሙሉነሽ ውበቴ እያጋጠሙ ካሉ ችግሮች ለመውጣት ማኅበረሰቡን የሚያማርሩ እና ለብልሹ አሠራር የሚዳርጉ አሠራሮችን በመቅረፍ ለፍትሕ መቆም ተገቢ ነው ብለዋል።
ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ ሙስና በተቋማት አሠራር ላይ ጫና ማሳደሩን የገለፁት የዞኑ ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ አወቀ ወጣቶች ብልሹ አሰራሮችን ለመፍታት ከተቋማት ጋር በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን “ወጣቶችን ያከበረ የፀረ- ሙስና ትግል የነገን ሰብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የውይይት መድረክ የተቋማት ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!