ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የጥራት መንደርን ጎበኙ።

24

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተመረቀውን የጥራት መንደር ጎብኝተዋል።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን ፣ የንግድ ሥርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ.ር) እና የጥራት መሠረተ ልማት ተቋማት አመራሮች ለፕሬዝዳንቱ ስለጥራት መንደሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

አቶ እንዳለው የጥራት መንደሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ አመንጪነት እንደተጀመረ በመግለጽ ለግንባታው 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትና ጥራትን የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የላብራቶሪና የቢሮ ግንባታ የያዘ መሆኑን ለፕሬዝዳንቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ.ር) በበኩላቸው የጥራት መንደሩ የገቢና ወጪ ምርቶችን ጥራት በማረጋገጥ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በጥራት መንደሩ የሚገኙ ተቋማት በጤና፣ በኮንስትራክሽን፣ በግብርና ውጤቶች፣ በምግብ እና በኢንዱስትሪ ግብዓቶች እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ገቢና ወጪ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ጥራት የሚያረጋግጡ የላብራቶሪ መሣሪያዎችን ተዘዋውረው በማየታቸው መደሰታቸውን ከንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፍትሕ የሚጀምረው የእያንዳንዱን ግለሰብ መብት ስናከብር ነው” ፊቶል ሲያኮር
Next articleበማኅበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ ለመከላከል ዝግጁ መኾናቸውን ሚሊሻዎች ገለጹ።