አርሶ አደሩ አምራች፤ የከተማ ነዋሪው ሸማች የኾነበት ልምድ በሌማት ትሩፋት መቀየር እንዳለበት ተገለጸ።

30

ደሴ፡ ታኅሳስ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አስተዳደር እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት በሌማት ትሩፋት 44 ሺህ ቶን ወተት ለማምረት እየሠራ መኾኑን ገልጿል። በወተት ምርት እና በልዩ ልዩ የከተማ ግብርና የተሰማሩ እና አሚኮ ያነጋገርናቸው ግለሰቦች እንደተናገሩት ሃብት አፍርቶ ራስን ከመለውጥ ባሻገር ለሌሎች የሥራ እድል እየፈጠሩ ይገኛሉ።

ቦታ እና የተያያዙ ችግሮችን እየተነጋገሩ መፍታት አስፈላጊ መኾኑን ያነሱት ነዋሪዎቹ በተገኘው አጋጣሚ ራስን መለወጥ ተገቢ መኾኑን ነው ያነሱት:: ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር ሁሉም ነገር በጓሮ ሲገኝ ለጤና ያለው ጥቅምም የጎላ መኾኑንም ገልፀዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የደሴ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ በአስተሳሰብ እና በተግባር ለመለወጥ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በተጀመሩ የሌማት ቱርፋት ሥራዎች ለውጦች መመዝገባቸውንም አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት በመንግሥት ልዩ ክትትል እና ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ነው ያሉት ኀላፊው የሚነሱ ችግሮችን በመፍታት ወጤት ማስመዝገብ ያስፈልጋል ብለዋል።

እስካሁን በነበረው የአሠራር ሂደት አርሶ አደሩ አምራች የከተማ ነዋሪው ሸማች የኾነበት አካሄድ መቀየር እና ከተሜውም ባለው አማራጭ አምራች መኾን ይጠብቃል ተብሏል። የሌማት ትሩፋት በሌላ መንገድ የሥራ ባሕልን መቀየሪያ መንገድ እንደኾነም አስረድተዋል።

በዛሬው ዕለት “ሁሉን በደጄ አመርታለሁ የተመጣጠነ ምግብ እመገባለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ በዘርፉ ከተሳተፉት ጋር የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

ዘጋቢ፦ ደጀን አምባቸው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ በራሱ አቅም የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እየሠራ ነው።
Next article“ፍትሕ የሚጀምረው የእያንዳንዱን ግለሰብ መብት ስናከብር ነው” ፊቶል ሲያኮር