ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምዕራብ ጉጂ ገላን ወረዳ የቡና ልማትን ጎበኙ።

47

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ገጹ ባወጣው መረጃ በምዕራብ ጉጂ ገላን ወረዳ ከዚህ ቀደም ታርሶ የማያውቅ መሬት በቀርቻንሼ ትሬዲንግ አማካኝነት ወደ ምርታማ የቡና እርሻ ስፍራነት ተቀይሯል። በቀርጫንሼ የለማው መሬት ሜካናይዝድ እርሻን በመጠቀም አመርቂ የሆነ በሄክታር የ60 ኩንታል ምርት የሚያስገኝ ነው።

በጉብኝቱ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቡና ችግኝ ተክለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleግንባታቸው የዘገዩ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
Next articleየኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት 350 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎችን አፀደቀ።