ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነት መደረጉን ገለጹ።

40

ባሕር ዳር: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ገጻቸው እንዳስታወቁት ዛሬ ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ዩሬችካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮቻች ዙርያ ተወያይተናል ብለዋል፡፡

በርካታ ዓመታትን የዘለቀውን የኢትዮ-ቼክ ግንኙነትን ለማጠናከር በረጅም ጊዜ የብድር ስምምነት እና በልማት ትብብር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ነው ያሉት፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ በተለይም የቼክ መንግሥት በቱሪዝም እና በዱር እንስሳት ጥበቃ ዙርያ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸውልኛል ብለዋል፡፡

በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለቱ ሀገራት ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጥራት ለሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ዋነኛ ተግባር ነው” ዶክተር መቅደስ ዳባ
Next articleበአማራ ክልል በጸጥታ ችግር የዘገዩ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ ነው፡፡