“ጥራት ለሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ዋነኛ ተግባር ነው” ዶክተር መቅደስ ዳባ

63

አዲስ አበባ: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጤና ሚኒስቴር ከኅዳር 30 እስከ ታኅሳስ 7/2017 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ቀን አከባበርን እና የወባ ወረርሽኝ ንቅናቄን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት በሁሉም ክልሎች እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ታህሳስ 03/2017 የጤና መሪዎችና ባለሙያዎች ከዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮች ጋር በመኾን ለኅብረተሰቡ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።

“ጥራት ለሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋን ዋነኛ ተግባር ነው” ያሉት ሚኒስትሯ የጤና መገልገያ ተቋማትን የዘመኑ እና በመድኃኒትና በባለሙያዎች የተደራጁ በማድረግ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከክልሎች ጋር በጋራ እየሠሩ መኾናቸውንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ቀናትም በጤናው ጉዳይ እየተሠሩ ባሉ እና በክፍተቶች ላይ የመንግሥት የሥራ ኀፊዎች እሰከ ወረዳ በመውረድ ከማኅበረሰቡ ጋር ውይይቶችን ያደርጋሉ ብለዋል።

ዶክተር መቅደስ በመግለጫቸው 48 ቀናት የሆነው የወባ ወረርሸኝ ንቅናቄን በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በንቅናቄው ሰዎችን ከወባ ወረርሽኝ የመከላከል እና የታመሙትንም የማዳን ተግባራት መሠራታቸውን ነው ያመላከቱት፡፡ ጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመኾን ሰፊ የሆኑ ሥራዎችን መሥራቱን ነው የተናገሩት፡፡

በንቅናቄው የጤና ኤክስቴንሽኖችን በማደራጀት ኅብረተሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ክፍተት የሚታይባቸውን ቦታዎች በመለየት የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶች ለማሟላት እየሠሩ መኾናቸውን ነው ያመላከቱት፡፡

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሙስና ሊጠፋ የነበረ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን የሰሜን ወሎ ዞን አስታወቀ።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነት መደረጉን ገለጹ።