በደብረ ማርቆስ ከተማ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ግንባታ ተጀመረ፡፡

75

ደብረ ማርቆስ: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሁለ ገብ የገበያ ማዕከል ሊገነባ መኾኑን ከተማ አሥተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በከተማዋ የሚገነባው የገበያ ማዕከል የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቾች ማቅረብ የሚያስችል ነው ፡፡ ሁለገብ የገበያ ማዕከሉ በከተማ አሥተዳደሩ እና በክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚገነባ ተመላክቷል፡፡ የዜጎችን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለተጠቃሚው ለማድረስ ያስችላል የተባለለት የገበያ ማዕከሉ ሥራም ተጀምሯል፡፡

ግንባታውን የተረከበው ተቋራጭ መንቆረር ኮንስትራክሽን ነው፡፡ በአጭር ጊዜ እና በጥራት ገንብቶ ለማስረከብ እንደሚተጋ የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን ደባስ ተናግረዋል፡፡ግንባታው ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል፡፡ የገበያ ማዕከሉ በአራት ወራት ይጠናቀቃልም ተብሏል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ተወካይ ኃላፊ ዮሴፍ መለሰ የገበያ ማዕከሉ ሲጠናቀቅ የገበያ መረጋጋትን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ የገበያ ማዕከሉ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቾች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማድረስ የሚያስችል መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ግንባታውም በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለአገልግሎት ይውላል ነው ያሉት፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበተሠሩ ሥራዎች 22 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ከምዝበራ መታደግ ተችሏል።
Next articleበሙስና ሊጠፋ የነበረ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን የሰሜን ወሎ ዞን አስታወቀ።