የሃራ ከተማ አሥተዳደር ለአካባቢው የጸጥታ ተቋም አባላት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

23

ወልድያ: 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

የሃራ ከተማ አሥተዳደር ለሰላም አስከባሪ፣ ለፖሊስ እና ለምርጥ 70 ሚሊሺያ አባላት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ነው። “ለልማት እንተጋለን፤ ለሰላም እጆቻችንን እንዘረጋለን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ሥልጠናው እየተሰጠ ያለው።

የሃራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ የገጠመውን የሰላም እጦት ችግር ለመቀልበስ የሠልጣኞች ሚና ወሳኝ መኾኑን ገልጸዋል።

ከንቲባው አክለውም የሃራ ከተማን አንፃራዊ ሰላም በማስጠበቅ የአካባቢያችንን ሰላም ለማረጋገጥ ትኩረት አድርገን ለመሥራት ሥልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በሃራ ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፈንታው በለጠ ሥልጠናው በአካልም ኾነ በሥነ ልቦና የተሻለ አቅም ለመገንባት የሚያስችል በመኾኑ ሠልጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

ሥልጠናው የሚሰጠው በሰሜን ምሥራቅ ዕዝ የ802ኛ ኮር የሥልጠና ክፍል መኾኑ ተመላክቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች 8 ሺህ ቤቶች ተገነቡ።
Next articleበተሠሩ ሥራዎች 22 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ከምዝበራ መታደግ ተችሏል።