በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች 8 ሺህ ቤቶች ተገነቡ።

59

አዲስ አበባ: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለልማት ተነሺዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች በ10 ቢሊዮን ብር ወጭ 8 ሺህ ቤቶች እንደተገነቡ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ይህን ያሉት በ10 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው እና ዛሬ የተመረቀው የገላን ጉራ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት እና የመኖሪያ መንደር ምረቃ ላይ ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አሥተዳደሩ ሰው ተኮር ሥራዎችን በመሥራት ለነዋሪዎች ምቹ እና የተደላደለ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር በኀላፊነት እየሠራ ነው ብለዋል።

እስካሁንም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በ10 ቢሊዮን ብር ወጭ 8 ሺህ ቤቶች እንደተገነቡም አስረድተዋል።

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት ተነሺዎች ካሳ መከፈሉን ያነሱት ከንቲባዋ ከ100 ሄክታር በላይ መሬት ደግሞ የምትክ ቦታ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በ60 ቀናት የግንባታ ሂደቱ እንዲጠናቀቅ በገንዘብ እና በሙያቸው ላገዙ ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleግብር ከፋዮች ከየካቲት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ ደረሰኝ እንዲጠቀሙ ተወሰነ።
Next articleየሃራ ከተማ አሥተዳደር ለአካባቢው የጸጥታ ተቋም አባላት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።