
ባሕር ዳር: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የተመራዉ ጥምር ጦር እራሱን “ፋኖ” ብሎ ከሚጠራዉ ፅፈኛ ቡድን በላይ ጋይንት ወረዳ የገጠር ቀበሌወችን እያፀዳ እንደሚገኝ ተገልጿል። ለ1 ዓመት ያህል በፀፈኛ ቡድኑ ሲዘረፍና ሲንገላታ የቆየዉን የዛጎችና የአከባቢዉን ማኅበረሰብ መታደግ መቻሉን የላይ ጋይንት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ግርማ ይስማዉ ተናግረዋል፡፡
የበዛጎች ከተማ እና ዙሪያዉ ያሉ ቀበሌወችን ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን ሕግ የማስከበር እና በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዉ ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዉን በበላይ እየመሩ የሚገኙት ዋና አሥተዳዳሪው በተሠራዉ የሕግ ማስከበር ሥራ ፅንፈኛ ቡድኑን በመደምሰስና በማሳደድ አካባቢዉን ነፃ ማድረግ ተችሏል። ፅፈኛ ቡድኑ ሲጠቀምባት የነበረዉን አንድ ኮብራ መኪና ፣ ለዘረፋ ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን እና ለምግብነት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ሬሽኖች መያዝ መቻሉን አሥተዳዳሪዉ ገልፀዋል፡፡
በአካባቢዉ ማኅብረተሰብላይ ፅፈኛ ቡድኑ አስነዋሪ ወንጀሎችን ሲፈፅም መቆየቱን የአካባቢዉ ነዋሪወች ገልፀዋል፡፡
በሕግ ማስከበር ሥራዉ ከወረዳ አስተባባሪ አመራሮች በተጨማሪ ሌሎች የቀጣናው የፓለቲካ አመራሮች ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን አካባቢዉን ከፅፈኛ ቡድኑ የማፅዳት ሥራ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ከአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
