
ባሕር ዳር: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲኾን እየሠሩ መኾኑ ተገልጿል።
አሁን ላይ ለዩኒቨርሲቲዎች ለምገባ የሚወጣውን ወጭ እና ገበያውን መሠረት በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት አድርጓል።
በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሠረት በተቋማቱ የምግብ ሥርዓቱ ተመሳሳይ እንዲኾን በባለሙያዎች ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ነው የተብራራው።
በትምህርት ሚኒስቴር የአሥተዳደር እና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ.ር) ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል።
ዶክተር ሰለሞን በሀገሪቱ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ያለው የአመጋገብ ሥርዓት ተቀራራቢ እንዲኾን እየተሠራ መኾኑንም ጠቅሰዋል።
በአዲሱ የበጀት ተመን መሠረትም ለዩኒቨርሲቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!