
አዲስ አበባ: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከ286 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የገላን ጉራ የተቀናጀ የልማት መንደር ዛሬ ተመርቋል።
በ60 ቀናት ተገንብቶ ለምረቃ የበቃው መንደሩ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ለካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የተገነባ ነው።
ገላን ጉራ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት እና የመኖሪያ መንደር በውስጡ 1 ሺህ 200 የመኖሪያ ቤቶችን የያዘ መኾኑ ተገልጿል።
ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ፋብሪካዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የንግድ ሱቆች እና ግዙፍ የአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራዎችን ይዟልም ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማው መሪዎች በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!