“ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደ አርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

25

ባሕር ዳር: ኅዳር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደ አርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው”ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንደ ሀገር የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለከተሞችም ሆነ ለገጠር አካባቢዎች ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ስለመኾኑም አንስተዋል። ዛሬ የጎበኙት አይነት የሙዝ ልማት ሥራዎችን በገጠር አካባቢዎች በማሳዎች ላይ የኩታ ገጠም እርሻ አሰራረን ጀምረናል ብለዋል። እነዚህን ጥረቶች የሚደግፈው የሌማት ትሩፋት ሥራ በየአርሶ አርብቶ አደሩ ቤት የእንቁላል ምርትን ከአሳ እና ከብት ርባታ ብሎም ንብ ማነብ ጋር ምርት በማሳደግ ላይ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህ መርሃግብሮች በጥምር የገጠሩ እና የከተማው ነዋሪዎች ከትሩፋቱ እንዲካፈሉ አልመው ሠርተዋል ነው ያሉት። በተለይ የኩታ ገጠም እርሻ በአርባምንጭ ታላቅ ተስፋ የሰነቀ ስለመኾኑም አረጋግጠዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለአቅመ ደካማ ወገኖች የተሻለ ኑሮ ለመፍጠር በጋራ መሥራት ይገባዋል” የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር)
Next articleራሱን “ፋኖ ” እያለ የሚጠራው ቡድን በግዳን ወረዳ የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ላይ ውድመት አደረሰ።