የጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ምህረት ጠይቀው ገቡ።

201

ደባርቅ: ኅዳር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ምህረት ጠይቀው ገብተዋል።

የታጣቂ ቡድኑ ሎጄስቲክስ እና ፋይናንስ ኀላፊ ነጋ አዛናው እና የቡድኑ ዘመቻ ኀላፊ ዋና ሳጅን ክብረት አያሌው የሰላም ጥሪውን በመቀበል ምህረት ጠይቀው ገብተዋል።

የጽንፈኛ ቡድኑ አመራሮች በተሳሳተ አጀንዳ ተታልለው ወደ ጫካ መግባታቸውን በማስታወስ በቀጣይም የበደሉትን ማኅበረሰብ ለመካስ ለሰላም እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የጦርነት ትርፉ ኪሳራ ነው ያሉት የቡድኑ አባላት በተሳሳተ አጀንዳ በመደናገር የወጡ አካላትም ቆም ብለው በማሰብ የሰላም ጥሪውን ተጠቅመው ወደ ማኅበረሰቡ ሊቀላቀሉ ይገባል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጻታዊ ጥቃን በመከላከል ሁሉም ኀላፊነቱን እንዲወጣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ አሳሰበ።
Next article“ሀገረ መንግሥታችን እንዲጸና እና ልማት አንዲፋጠን ብሔር ብሔረሰቦች ለሰላም ሊሠሩ ይገባል” አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር