በተሳሳተ መንገድ የጽንፈኛ ቡድኑ አባል ኾነው ሕዝባቸውን ሲበድሉ የቆዩ ከ300 በላይ ታጣቂዎች በይቅርታ ተመለሱ።

22

ባሕር ዳር: ኅዳር 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን በበርካታ ቀበሌዎች እና ወረዳዎች በማኅበረሰቡ ፍላጎት የሰላም ውይይቶች ተካሂዷል።

ውይይቶችን ተከትሎም በተሳሳተ መንገድ የጽንፈኛ ቡድኑ አባል ኾነው ሕዝባቸውን ሲበድሉ የቆዩ ከ300 በላይ ታጣቂዎች በይቅርታ መመለሳቸውን የዞኑ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ገብረሥላሴ ታዘብ ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ በጫካ ቆይታቸውም ሕዝብ እና መንግሥትን መበደላቸውን በመገንዘባቸው መመለሳቸውን ነው መምሪያ ኀላፊው ለአሚኮ የገለጹት።

መምሪያ ኀላፊው መንግሥት በይቅርታ የተመለሱ ታጣቂዎች ሕዝባቸውን እንዲክሱ ለማስቻል ወደ መደበኛ ሕይዎታቸው እየመለሰ ስለመኾኑም ነው ያብራሩት።

ሌሎች በተሳሳተ መንገድ የጥፋት መንገድን እየተከተሉ ያሉ ታጣቂዎችም በይቅርታ ተመልሰው ወደ ማኅበረሰቡ በመቀላቀል ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲጀምሩ ነው ያስገነዘቡት።

እስካሁን ያደረሱትን ጥፋትም በልማታዊ ሥራ እንዲያካክሱ አቶ ገብረሥላሴ ታዘብ አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የፀና ሀገር ለመገንባት የጋራ ትርክት ያስፈልገናል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleበኮሪደር ልማቱ የተነሱ የኮንቲነር ባለይዞታዎችን መልሶ ለማቋቋም እየሠራ መኾኑን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።