
ባሕር ዳር: ኅዳር 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ 43 ግለሰቦች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ አማራጭን ተቀብለው በይቅርታ ተመልሰዋል።
ግልሰቦቹ ሳይገባቸው በአልባሌ ድርጊት ሲሳተፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ድርጊታቸው ስህተት፣ ለሀገር እና ለሕዝብም የማይጠቅም መኾኑን በመገንዘብ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አምራጭ ስለመቀበላቸውም ተናግረዋል።
የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመላክተው እነዚህ ግለሰቦች ታጥቀው ሲበድሉት የቆዩትን ማኅበረሰብ ለመካስ ስለመዘጋጀታቸውም አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!