
አዲስ አበባ: ኅዳር 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 2ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የባሕልና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ከጥር 15 እሰከ 18/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።
የፌስቲቫሉን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ከምሥራቅ አፍሪካ ባሕል ፌስቲቫል ተሳታፊዎች ጋር ተወያይቷል።
የኬንያ፣ የጅቡቲ እና የሱዳን ኤምባሲ ተወካዮች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል። የውይይቱ ዋና አላማም ለፌስታቫሉ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች ለመለየት ነው።
የባሕል ፌስቲቫሉ አሥተባባሪ አሕመድ መሐመድ እንዳሉት ከ3 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጀው 1ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል የሀገራቱን ትስስርና የባሕል ተውውቅ ያጎለበተ ነበር። ፌስቲቫሉ በተከታታይ መዘጋጀቱ እየጎለበተ የመጣውን አንድነትን ለማጠናከር አስተዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የፌስቲቫሉ ተሳታፊና አዘጋጅ መሆኗ ያላትን የባሕል ጥልቀት አጉልታ ለማውጣት መልካም አጋጣሚ ስለመኾኑም አስተባባሪው ተናግረዋል። በባሕል እና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግም እንደሚረዳ አንስተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!