“የአንዳችን ሃይማኖት ፣ ባሕል እና ቋንቋ ለሌሎቻችን ውበታችን ነው” አፈ ጉባኤ ጋሻው አራጋው

7

ባሕር ዳር: ኅዳር 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ)19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ የዞኑና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች እና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈዋል።

የክብረ በዓሉ ተሳታፊ ልዑልሰገድ አሰፋ ኢትዮጵያ ባለብዙ ባሕል መኾኗን ተናግረዋል። ባሕላችን ጠብቀን እና ተንከባክበን ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ ይገባናል ነው ያሉት። ሌላኛው ተሳታፊ ገናነው ተካ የተለያየ አስተሳሰብ እና አመለካከት ቢኖረንም በባሕል እና በሃይማኖት ግን አንዱ ብሔር ከሌላው ብሔር እኩል ነው ብለዋል።

የገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አብዱልከሪም ሙሐመድ በመቻቻል እና በመግባባት ለሀገራዊ ግንባታ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ነው ያሉት። የምዕራብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ እርጥባን መስፍን ልዩነቶችን በመተው፣ አንድነታችን በማበልጸግ ለሀገራዊ ሰላም እና ልማት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጋሻው አራጋው የበዓሉ ዋና ዓላማ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለማጠናከር ነው ብለዋል። ሁሉም ብሔር እኩል ነው ያሉት አፈጉባኤው ስንከባበር አንድ የኾነ የጋራ መግባባት ላይ እንደርሳለን ነው ያሉት። “የአንዳችን ሃይማኖት፣ ባሕል እና ቋንቋ ለሌሎቻችን ውበታችን ነው” ብለዋል።

የበዓሉ መከበር አደኛው ለሌላኛው ባሕሉን ለማስተዋወቅ ፋይዳው ትልቅ መኾኑን ነው የተናገሩት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከሙስና የጸዳ ሀገር እና ትውልድ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ኅብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆን ተጠየቀ።
Next article“ጽንፈኛው ቡድን በፈረስ ቤት 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው