
ባሕር ዳር: ኅዳር 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ለመታደም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል።
አፈጉባኤው አርባምንጭ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፀሐይ ወራሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት እንደሚከበር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!