የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስት ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ።

73

ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ሥስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።

የመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያ ሕንፃዎች ረቂቅ አዋጅ ነው። ረቂቅ አዋጁ በነባሩ ሕግ በአፈፃጸም የተለዩ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን የሚፈታ፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች የሚቀርፍ፣ ግልጽና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል መኾኑ ተመላክቷል።

በሁለተኛነት የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ነው በምክር ቤቱ የጸደቀው። የሪል እስቴት ልማቱ አቅርቦት ወደኋላ የቀረ፣ የሕዝብን ፍላጎት የማያሟላ ይሄን ማሻሻል ማስፈለጉ ተገልጿል። የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ሥርዓቱ ዘመናዊ፣ በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል። በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግሥትን ጥቅም የሚያሳጣ እንዳይሆን ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ ነው ተብሏል።

ሌላኛው በምክር ቤቱ ያጸደቀው የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ ማሻሻያ አዋጅን ነው።

የጸደቁት አዋጆች የነበሩ ችግሮችን የሚፈቱና የተሻላ ሥራ እንዲሠራ እንደሚያደርጉ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገርን ወደ ልዕልና የሚያሸጋግሩ ተተኪ አመራሮችን የማፍራት ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleየኢንቨስትመንት ዘርፍን ለማነቃቃት እየሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስታወቀ።