“ሀገርን ወደ ልዕልና የሚያሸጋግሩ ተተኪ አመራሮችን የማፍራት ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

56

ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሀገር በቀል እና ችግር ፈቺ የአመራርነት ብልሃትን የምንቀስምበት እንዲሁም ትብብር እና ወንድማማችነትን የምናጎለብትበት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሚሳተፉበት “ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ”ን አስጀምረናል ብለዋል፡፡

የነገ መሪዎችን መገንባት የሚጀምረው ዛሬ በሚሠራ ሥራ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ማለት በትውልዶች መካከል የመሪነት ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ክህሎት እና የተግባር ቁርጠኝነትን ለመታጠቅ በነባሩና በተተኪ ወጣት አመራሮች መካከል የዕውቀት እና የልምድ ሽግግር ማረጋገጥ ይጠይቃል።

የዛሬው ጉባኤ ከአንድ ክስተት በላይ የኾነ የተግባር ምልክት ነው፡፡ በመኾኑም መሪዎቻችንን ብሔራዊ ግቦቻችን ለመምራት የሚያስፈልጋቸውን ዕውቀትና መሳሪያዎች ለማስታጠቅ እንዲሁም መሪነት በዋናነት ለማገልገል የሚወሰድ ሃላፊነት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

ስለዚህም ሀገራችንን ወደፊት ለማራመድ አቅም የሚሆኑ መሪዎችን ለማፍራት እና ለመቅረጽ የአብሮነት ህብረታችን መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዘሊንክ ምንድን ነው?
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስት ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ።