በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ቀጣና የሰላም አስከባሪ እና የሚሊሻ አባላት ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

31

ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ቀጣና የሰላም አስከባሪና የሚሊሻ አባላት ሥልጠና በፍኖተ ሰላም ከተማ እየተሠጠ ነው።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ሙሉጌታ ዓለም በሁሉም አካባቢ የጸጥታ መዋቅሩን ለማጠናከር እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። ከየቀበሌው ለተመለመሉ ምርጥ 70 ሚሊሻዎች ሥልጠና እየወሰዱ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

ሠልጣኞች ከተደራጀው የጸጥታ መዋቅር ጋር በመኾን የአካባቢያቸውን ሰላም ያስጠብቃሉ ነው ያሉት።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ ባለፈው አንድ ዓመት በዞኑ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር መከሰቱን ተናግረዋል። ከየቀበሌው የተመለመሉ ሚሊሻዎች ሥልጠና ወስደው አካባቢያቸውን እንደሚጠብቁም አመላክተዋል። የአካባቢን ሰላም የሚያስጠብቅ የጸጥታ ኃይል እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

ከፍኖተ ሰላም ከተማ ኮምዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የክልል፣ የዞን፣ የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአካል ጉዳተኞች እኩል ተጠቃሚ እንዲኾኑ ሊሠራ ይገባል።
Next articleንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ አስጀመረ።