የአካል ጉዳተኞች እኩል ተጠቃሚ እንዲኾኑ ሊሠራ ይገባል።

44

ደብረ ብርሃን: ኅዳር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን የአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጌታሰው ፈንታሁን የአካል ጉዳተኞችን እኩል ተጠቃሚ የማድረግ ተግዳሮቶች መኖራቸውን አንስተዋል።

አቶ ጌታሰው አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ የግንዛቤ ችግሮች መኖራቸውን አንስተው በተለይ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ አካል ጉዳተኞች ችግር የከፋ መኾኑን አንስተዋል። ይህንን የአመለካከት ችግር ለመቅረፍ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

የሰሜን ሽዋ ዞን ሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ የሮምነሽ ጋሻውጠና አካል ጉዳተኞችን አካቶ መብታቸውን ማክበር ቀዳሚ ጉዳይ በመኾኑ ትኩረት ተሠጥቶ ይሠራል ብለዋል።

አካል ጉዳተኞችን በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኋላ ሳይቀሩ በተለያዩ ዘርፎች እንዲሳተፉ በማድረግ እኩል ተጠቃሚ እንዲኾኑ መሠራት እንዳለበትም ነው የተጠቆመው።

በሰሜን ሸዋ ዞን “የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታች እና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ መልዕክት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና የሕጻናት ቀን እየተከበረ ነው። ቀኑ ሲከበር አካል ጉዳተኞች፣ ታዳጊዎች እና አጋር ተቋማት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡- አበበች የኋላሸት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማዕቀፎች የዲጂታል ልማቱን ለማሳካት በርካታ ሥራዎች መሥራታቸው ተገለጸ፡፡
Next articleበምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ቀጣና የሰላም አስከባሪ እና የሚሊሻ አባላት ሥልጠና እየተሰጠ ነው።