
ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ ምክንያቶች ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች እና ሕጻናት በአንድ ማዕከል አርፈው አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል በባሕር ዳር ከተማ ሊገነባ ነው።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ፣ የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አስቀምጠዋል።
ማዕከሉ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲኾን በ123 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደሚገነባ ተነግሯል።
በጀቱ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል የተገኘ ሲኾን ዲዲሲ የተባለው የክልሉ የልማት ድርጅት ግንባታውን ያከናውናል።
ግንባታው ከአንድ ዓመት ባጠረ ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚውልም ተገልጿል።
ማዕከሉ ሥራ ሲጀምር ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች እና ሕጻናትን በመቀበል የጤና፣ የሥነ ልቦና፣ የኢኮኖሚ እና የፍትሕ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ለመስጠት ያስችላል ነው የተባለው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!