
ደብረ ብርሃን: ኅዳር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የዓለም ኤች አይ ቪ ኤድስ ቀንን አክብሯል። የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሥራ አሥኪያጅ የሽጥላ ሙሉጌታ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዉ በሚጠበቀዉ ደረጃ ባለመኾኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በግዙፍ የግንባታ ቦታዎች ላይ የቫይረሱ ስርጭት እንዲጨምር ምክንያት መኾኑን ተናግረዋል።
የወጣቶችን እና የአምራች ወገኖችን ሕይወት የሚቀጥፈዉን ቫይረስ ለመከላከል ቀጣይነት ያለዉ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። ኢንዱስትሪ ፓርኩ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ አልሚዎች እና ሠራተኞች የሚገኙበት በመኾኑ እለቱን አስታዉሶ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሥራትም ያስፈልጋል ነዉ ያሉት።
የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ እንደሚያሳየዉ በየዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች በአዲስ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ይያዛሉ ። በእለቱም “የሴት ጥቃት የእኔም ጥቃት ነዉ!” በሚል መሪ ሃሳብ የነጭ ሪቫን ቀንም ተከብሯል።
ዘጋቢ:_ ብርቱካን ማሞ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!