ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደጀኔ ልመንህ ተናገሩ፡፡

68

ደሴ: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ በከተማዋ ነዋሪዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የጸጥታ ኀይሉ ቀን ከሌሊት መሥራቱ በውይይቱ ተነስቷል፡፡ ይህንንም አጠናክሮ ማስቀጠል እና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከፍተኛ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉ ተነስቷል፡፡

ያነጋገርናቸው የፖሊስ እና የሚሊሺያ አባላት ከተማዋ ሰላም እንድትኾን እና ዜጎች የዕለት ከዕለት የልማት ሥራዎቻቸውን እንዲከውኑ ጥረታቸውን እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰዒድ አሊ በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለማቃለል ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመግባባት ከተማዋ ሰላሟ እንዲጠበቅ ሥራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት፡፡

ማኅበረሰቡ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መደረጉን የገለጹት መምሪያ ኀላፊው በቀጣይም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡ የአማራ ክልል ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደጀኔ ልመንህ የክልሉ የጸጥታ መዋቅር በዓላማ ጽናት ችግሮቹ እንዲፈቱ ተጋድሎ እያደረገ መኾኑን ነው ያነሱት፡፡

በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በጸጥታ ኀይሉ ላይ በትኩረት እየተሠራ እንደኾነ ምክትል ቢሮ ኀላፊው ተናግረዋል፡፡

በደሴ ከተማ የሚገኘው የጸጥታ ኀይል ከተማዋን ሰላም በማድረግ ሒደት ውስጥ ሚናው ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል። ውይይቶች እና ምክክሮች በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሥልጠና የወሰዱት የመንግሥት እና የግል ታጣቂዎች ከተማቸውን ለመጠበቅ ዝግጁ መኾናቸውን ገለጹ።
Next article“የደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራው በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል” ዣንጥራር ዓባይ