የንግዱ ማኅበረሰብ ሕግን አክብሮ በመሥራት ኀላፊነቱን እንዲወጣ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ አሳሰቡ።

19

ደብረ ማርቆስ: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ ከንግዱ ማኅበረሰብ ከተውጣጡ ነጋዴዎች ጋር ምክክር አካሂዷል።

የደብረማርቆስ ከተማ በጸጥታው መደፍረስ ምክንያት የንግድ እንቅስቃሴው ተቀዛቅዞ ቆይቷል። አሁን ላይ በተገኘው አንጻራዊ ሰላም የተቀዛቀዘውን የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት ለመመለስ እና ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ውይይት አድርገዋል።

ሰላም ለንግድ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመኾኑ መንግሥት እና የንግዱ ማኅበረሰብ በሰላም ጉዳይ በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባም የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ አስገንዝበዋል።

በጸጥታው መቃወስ ከተማዋን ለቀው የሄዱ ነጋዴዎችም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ ጥሪ አድርገዋል።

የንግዱ ማኅበረሰብ አባላትም የተከሰተው የጸጥታ ችግር በሥራቸው ላይ ጫና የፈጠረ በመኾኑ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኀላፊ የኔሰው መኮንን ልማት የሚረጋገጠው ነጋዴው በሚከፍለው ግብር በመኾኑ የንግዱ ማኅበረሰብ ለሰላም መረጋገጥ መተባበር እና ሕግን የተከተለ የንግድ ሥርዓት መፍጠር ይገባዋል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጤናማ ሀገርን ለመገንባት ጤናማ ትውልድን መፍጠር የሁሉም ኀላፊነት ሊኾን ይገባል” ጤና ሚኒስቴር
Next article“የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕዝቡን የጤና ስጋት በመለየት ምላሽ እየሠጠ ነው” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)