“በቀጣይ የሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በትኩረት ይሠራል” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ

38

ጎንደር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ክልላዊ የመጠቃለያ ዝግጅት በጎንደር እየተካሄደ ነው።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የፌደሬሽን ምክር ቤትን እቅድ እንደ መነሻ በመውሰድ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ሥራዎችን ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ኮሚቴዎችን በማዋቀር የሕገ መንግሥት አስተምሮን በትምህርት ቤቶች በጥያቄ መልስ እና በተለያዩ ኩነቶች የግንዛቤ ፈጠራ ማካሄዳቸውንም ገልጸዋል። በክልሉ የፌደራሊዝም ሥርዓቱን መሠረት በማድረግ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ሲከበር መቆየቱንም አስታውሰዋል።

በክልሉ ከወረዳ ጀምሮ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በደም ልገሳ፣ ማዕድ በማጋራት፣ ከአፋር ክልል ሕዝብ ጋር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በማድረግ፣ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ሲከበር መቆየቱንም ተናግረዋል።

ቀኑን ከማክበር ባለፈ በቀጣይ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር፣ የማዕድ ማጋራትን ለማስቀጠል፣ የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን በይበልጥ ይሠራል ነው ያሉት።

በጎንደር ከተማ በተካሄደው ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር የተገኙ የፌደራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ተመስግነዋል።

ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጸረ ሙስና ቀን በዓልን ከማክበር ባለፈ በቁርጠኝነት ሙስናን መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
Next articleየአገልግሎት አሰጣጥ አሠራሮችን እያዘመነ መኾኑን የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን አስታወቀ።