የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት አራተኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

34

ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ በሶስተኛ መደበኛ ስብሰባው እንዲፈፀሙ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች መሠረት የተሠሩ ሥራዎችን እና አስፈላጊ የሆኑ የኮሚቴ አደረጃጀቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ለዲጂታል ኢትዮጵያ አስፈላጊ የሆኑ የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክ ስትራቴጂ እና የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክ ንግድ ስትራቴጂ ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት አስታውቀዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ የሚያድግበት ዘመን ላይ እንደመሆኑ ምክር ቤቱም ለዚሁ ዕድገት ተገቢውን ሚና ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article📢 አብረውን ይሥሩ ! 📻
Next article“ብዝኅነት በአግባቡ ከተስተናገደ ለሀገራዊ መግባባት እና ለኅብረ ብሔራዊነ አንድነት መሠረት ነው” አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር