
ጎንደር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በጎንደር እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓሉ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የወል ትርክትን በማጽናት እና የኢትዮጵያን አንድነት በማስቀደም በአፍሪካ ቀዳሚ ለመኾን መሥራት ይገባል ብለዋል።
የአማራ ክልል ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር ተጣምሮ የሀገርን አንድነት ያስጠበቀ መኾኑንም ገልጸዋል። ወንድማማችነትን ለማጠናከር የማዕድ ማጋራት፣ የደም ልገሳ በማድረግ፣ የልማት ሥራዎች በመጎብኘት እና በመደገፍ በኩል በቁርጠኝነት ተሠርቷል ብለዋል።
የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በዓልን በማስመልከት ብቻ ሳይኾን ቀጣይነት ያለው የሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር መሥራታቸውንም ተናግረዋል። በበዓሉ ለመታደም ከሌሎች ክልሎች የመጡ እህት እና ወንድሞቻችን የሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በአብሮነት ልንሠራ ይገባል ነው ያሉት አፈ ጉባዔዋ።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!