
ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የአማራ ክልል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሔደ ነው። በመድረኩ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጎንደር ከተማ ከ300 ዓመታት በላይ የመንግሥታት ሥሪት ያላት ከተማ ናት ብለዋል።
ጎንደር የፈርጀ ብዙ ሥልጣኔ ማሳያ ከተማ መኾኗን የጠቀሱት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በአብሮነት ተጋምዶ የኖረ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ እንደኾነች ገልጸዋል። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሥልጣኔ ማማ ላይ የወጣች ከተማ እና የሥልጡን መኖሪያ የኾነችው ጎንደር በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሚገጥሙ ፈተናዎችን ተነጋግሮ መፍታት ይጠበቅባታል ብለዋል።
ጎንደርም ኾነ መላው አማራ ሌሎች ወገኖችን በማክበር እና በዕኩልነት በማስተናገድ የሚታወቅ ሕዝብ መኾኑን ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!