በባሕር ዳር ከተማ የነባር እና አዲስ ሚሊሻ አባላት ስልጠና ተጀምሯል።

44

ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መሪዎች እና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመኾን ስልጠናውን አስጀምረዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ስልጠና የተገኛችሁ ነባር እና አዲስ ሰልጣኝ የሚሊሻ አባላት የአካባቢን ሰላም ለማስጠበቅ ኀላፊነት ተጥሎባችኋል ብለዋል።

የከተማዋ ሕዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ፣ ሰርቶ እንዲለወጥ እና ልማት እንዲፋጠን አደራ ተጥሎባችኋል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleህፃናት ትምህርት ቤት እንዲሄዱ፣ ሴቶችም ከጥቃት እንዲጠበቁ ሰላምን ማጽናት ይገባል።
Next article“የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ከ33 በመቶ በላይ የእናቶችን ሞት ይቀንሳል” አብዱከሪም መንግሥቱ