
ወልድያ: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ የህፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የነጭ ሪባን ቀን በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው።
የመንግሥት ፖሊሲ ሰው ተኮር በመኾኑ ቀኑን አስቦ ከመዋል ባሻገር የህፃናት፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ጉዳይ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ አሁን ላይ ባለው የፀጥታ ችግር በሰሜን ወሎ ዞን ብቻ 274 ሺህ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ርቀዋል። ሴቶችም ለወሲባዊ ጥቃት ተጋለጭ ኾነዋል ነው ያሉት።
የዚህን ችግር ምንጭ ለማድረቅ የክልላችንን ሰላም ማፅናት ግድ በመኾኑ በትብብር ልንሠራ ይገባል ብለዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሴቶች፣ ህፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ እመቤት ደሳለኝ ሥርዓተ ፆታ ላይ የሚታየውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር በርካታ ሥራዎች እየሠሩ ነው ብለዋል።
በመኾኑም የህፃናት፣ የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የሁሉም በመኾኑ ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል ሲሉ አሳስብዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!