
ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መልካሙ አብቴ (ዶ.ር) እና ሌሎችም መሪዎች ናቸው በኢንስቲትዩቱ ተገኝተው ሥራውን እየተመለከቱ የሚገኙት።
የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የክልሉን ሕዝብ ጤና ቀድሞ በመጠበቅ እና ለኅብረተሰብ ጤና አስጊ የኾኑ በሽታዎች ሲከሰቱም ፈጥኖ በመቆጣጠር በኩል ከፍተኛ ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ኢንስቲትዩት ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!