
ጎንደር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ክልላዊ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን የማጠቃለያ ዝግጅት በጎንደር ከተማ ይከበራል። በዓሉን ለማክበር የፌዴራል እና የክልል መሪዎች ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል መሪዎች በክልል ደረጃ ለሚከበረው ማጠቃለያ በዓል ጎንደር ለመታደም ከተማ ገብተዋል።
ጎንደር ከተማ ሲገቡ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እናትነሽ ዋለ፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሪ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም ከከተማዋ የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!