
ጎንደር: ኅዳር 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን የአማራ ክልል የማጠቃለያ በዓል በጎንደር ከተማ ይከበራል።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በክልል ደረጃ ለሚከበረው ማጠቃለያ ክብረ በዓል ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
አፈ ጉባዔዋ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እናትነሽ ዋለ፣ የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በክልል ደረጃ ለሚከበረው ክብረ በዓል የሌሎች ክልሎች አፈ ጉባኤዎች እና ሌሎች እንግዶች እንደሚገኙ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈጉባዔ እናትነሽ ዋለ ገልጸዋል።
በማጠቃለያ ክብረ በዓሉ ጎን ለጎን በከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ጉብኝት እና ሌሎች መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም ተናግረዋል። በዓሉን እንግዳ ተቀባይነትን እና አብሮ መኖርን በሚያሳይ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!