ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሕጻናት፣ አረጋዊያን እና ሴቶች ዙሪያ እየተሠሩ ባሉ መልካም ተግባራት ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መከሩ፡፡

35

ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከሜሪ ጆይ የሥራ ኀላፊዎች ጋር መክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራች እና ዋና የሥራ አሥኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፣ ከሜሪ ጆይ ቦርድ ሠብሣቢ ይስማሽዋ ስዩም እና ከቦርድ አባላት ጋር ነው የመከሩት፡፡

በምክክራቸውም ሜሪ ጆይ በሕጻናት፣ አረጋዊያን እና ሴቶች በትምህርት፣ በጤና እና በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ በሠራው መልካም ተግባሮች ላይ መምከራቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቀለብ የመስጠት ግዴታ!
Next articleበደብረ ማርቆስ ከተማ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲጀምሩ እየተሠራ ነው።