
ጎንደር: ኅዳር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር አሁን ያለውን የሠላም ኹኔታ የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከዘጠኝ መቶ በላይ ወጣቶች ተመርቀው ወደ ሥራ ገብተዋል።
ወጣቶቹ ለአስራ አምስት ቀናት የሙያ እና የጽንሰ ሀሣብ ሥልጠና የወሰዱ ናቸው። በጎንደር ከተማ የሚስተዋሉ የዝርፊያ፣ የግድያ እና የእገታ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በየቀበሌዎቹ ለመሠማራት ዝግጁ መኾናቸውን ወጣቶቹ ተናገረዋል።

ወጣቶቹ በከተማዋ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ ናቸው። ከጉብኝት በኋላ የሥልጠና ማጠቃለያ መድረክ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!