“በኅብር ላይ የተመሰረተ አንድነት እና ሀገራዊ መግባባት መፍጠር ይኖርብናል” አምባሳደር ተፈራ ደርበው

45

ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ቤጂንግ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሚስዮን ተከብሯል።

ዘንድሮ “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ቻይና የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት እና የሚስዮኑ ሠራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሚስዮኑ መሪ ባለ ሙሉስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው በኅብር ላይ የተመሰረተ አንድነትና ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር የሀገራችንን ብልፅግና እና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።

ለበዓሉ በተዘጋጀው የመወያያ ሰነድ መነሻነትም ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የምንፈልገውን ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ እንዲሁም በቂ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር እኩልነትና ፍትሀዊነትን የተመረኮዘ ስርዓት መዘርጋት ለነገ የማይባል የቤት ሥራ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ምሁራን የሀገራችንን ባሕል እና እሴት እንዲሁም ኅብረተሰባዊ ትስስር መሰረት ያደረጉ አስተሳሰቦችን በማስረፅ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና መግባባት ለመፍጠር የላቀ ድርሻ እንዳላቸው መመላከቱ ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየትምህርት እና የሃይማኖት ተቋማት ግብረ ገብነት ላይ ትኩረት አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ።
Next articleሳምንቱ በታሪክ