
ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የአድማ መከላከል እና የ33ኛ ዙር በመደበኛ ፖሊስ የተመዘገቡ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶች ወደ ማሠልጠኛ በመግባት ላይ መሆናቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ መረጃ ያመላክታል።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ውሥጥ ከሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው ማስታወቂያ የአድማ መከላከል እና የ33ተኛ ዙር የመደበኛ ፖሊስ ምልመላ ያለፉ ወጣቶች ተመዝግበው የመመልመያ መስፈርቱን ያሟሉ የአድማ መከላከል ምልምል የፖሊስ አባላት ወደ ማሠልጠኛ ቦታ በመግባት ላይ መሆናቸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ልጅ አዱኛ ሙሉጌታ ገልፀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ምልመላው በተያዘለት ዕቅድና ጊዜ መሠረት በጥራት እንዲከናወን በየደረጃው ያላቋረጠ ጥረት ላደረጉ አመራሮችና ባለሞያዎችን አመሥግነዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!