ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በአል ተካሄደ።

32

ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመሥገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ፣የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልል ርእሳነ መሥተዳደሮች እና የከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም የፓርቲውና የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው የተከበረው ።

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በአል “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።

በአሉ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ በፓናል ውይይት፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በደም ልገሳ፣ በማስ ስፖርት፣ በፎቶ አውደ ርዕይ፣ በከተማ ጽዳት እና በሌሎችም ተግባራት ሲከበር ቆይቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታወቁ።
Next articleከምሥራቅ ጎጃም ዞን የተመለመሉ ወጣቶች ወደ ፖሊስ ማሠልጠኛ እየገቡ ነው።