ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታወቁ።

87

ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ በአምስት ዓመታት ጉዞው በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ የአፍሪካ ግዙፉ ፓርቲ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታውቀዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ሀገራዊ ማጠቃለያ መርሀ ግብር ዓድዋ መታሳቢያ ሙዚየም ተካሄዷል፡፡

በወቅቱ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እንደገለጹት፤ ብልፅግና ኢትዮጵያ ከድህነትና ከችግር እንድትወጣ ሌት ተቀን የሚሰራ ፓርቲ ነው። ፓርቲው አባላቱና መላውን ሕዝብ በማስተባበርና በማሳተፍ ሁለተናዊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

ብልጽግና ራዕያችንን እንድናሳካ፤ ህልማችንን እና ችግሮቻችንን ፈትተን እንድንሠራ የሚያደርገን ጉልበታችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላው ኢትዮጵያዊያን የወል እውነታችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና መለያው እውነት፣ እውቀትና ጥበብ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያን የላቀ ከፍታ ላይ ለማድረስ ሙሉ ዕይታ ያለውና በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በኮሪደር ልማት፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች የሚጨበጡና የሚታዩ ስኬቶችን ባለፉት አምስት ዓመታት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል፡፡

ኢፕድ እንደዘገበው ብልጽግና ፓርቲ 15 ነጥብ 7 ሚሊዮን አባላት ያሉት የአፍሪካ ግዙፉ ፓርቲ ነውም ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመገጭ ፕሮጀክት ለውጥ ከተደረገበት በኃላ በጥሩ መንገድ እየተሠራ ነው” አብርሃም በላይ (ዶ.ር)
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በአል ተካሄደ።