
ጎንደር: ኅዳር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር)፣ የክልል እና የጎንደር ከተማ የሥራ ኀላፊዎች የመገጭን ፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር) የመገጭ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ መቆየቱን አንስተዋል።
የፕሮጀክቱ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ግን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መኾኑን ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቱ የነበሩበትን የጥራት፣ የመዘግየት እና የፕሮጀክት አሥተዳደር ችግሮችን ሳይንሳዊ በኾነ መንገድ መፈታታቸውን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ፕሮጀክት መሥራት የሚችል ተቋራጭ እንዲገባ ተደርጎ ሥራው በጥብቅ ቁጥጥር እየተመራ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን በሠሩ አማካሪዎች አማካይነት መስተካከል ያለበት እንዲስተካከል እና መቀጠል ያለበት ተሻሽሎ እየተሠራ ነው ተብሏል።
ለፕሮጀክቱ ሥራ በርካታ ማሽነሪዎችን በማስገባት እየተሠራ መኾኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ የጎደሉ ነገሮችም በፍጥነት ይሟላሉ ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!