”ለመስኖ ልማት ሥራ ሜካናይዜሽንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

33

ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን ለአርሶ አደሮች የእርሻ ትራክተር ርክክብ ተደርጓል። በዕለቱ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የመስኖ ስንዴ ልማት ንቅናቄ ሥራም ተጀምሯል።

በሥነ ሥርዓቱ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በክልሉ የመስኖ ስንዴን ለማልማት እና በሌሎችም ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ሥርጭት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ከዚህ በፊት ከ13 በላይ ኮምባይነሮች መሠራጨታቸውንም ጠቅሰዋል። ዛሬ ደግሞ ለሰሜን ጎጃም ዞን 13 ትራክተር ማስረከባቸውን ነው የተናገሩት። ዛሬ ትራክተሮቹን ፈትኖ ለማስረከብ እና የመስኖ ስንዴ ልማትን ለማስጀመር መገኘታቸውን ዶክተር ድረስ አስረድተዋል። በዕለቱ በተለያዩ ዞኖች በንቅናቄ የመስኖ ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል።

በተያዘው ዓመት በመስኖ ስንዴ ልማት ከፍተኛ የስንዴ ምርት እንደሚመረትም ጠቅሰዋል። የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር አለመኖሩን የተናገሩት ዶክተር ድረስ የውኃ እጥረት እንዳይገጥምም ዝግጅት እየተደረገ ስለመኾኑ ነው ያብራሩት። ለውኃ መሳቢያ ሞተር የነዳጅ ችግር እንዳይገጥም ከንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር እየተነጋገሩ እንደኾነም ጠቁመዋል።

አርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ፍላጎት መኖራቸው ለልማቱ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ዶክተር ድረስ ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የተመለመሉ ወጣቶች ተሸኙ።
Next articleየአማራ ክልል ጤና ቢሮ አገልግሎቱን ለማሻሻል የባለሙያዎችን የመፈጸም አቅም የማሳደግ ሥራ እየሠራ ነው።