
ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአፋር ክልል ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቶ ዛሬ በሰመራ ከተማ ክልል አቀፍ የማጠቃለያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ አስያ ከማል፣ የአፋር ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሐመድ ሀሰን፣ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱሩህማን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ዘይና አልቃድርና የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አያን አብዲ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
“ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ የሚገኘው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የሕዝቦችን አብሮነት ለማጽናት ፋይዳው የጎላ ነው።
በክልላዊ ማጠቃለያ መርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ እና የክልሉ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፈ ሲሆን የሁለቱን ሕዝቦች የቆየ ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚያስችል ከአማራ ክልል ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!