የአየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው።

17

ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ ቀን በዓል “የተከበረች ሀገር የማይደፈር አየር ኃይል” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ዛሬ ማለዳ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀዋል።

ደረጃቸውን የጠበቁ የሠራዊቱ መኖሪያ ቤቶች፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የፓይለቶች መኖሪያ፣ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ምረቃ ተከሂዷል።

ከዚህ በተጨማሪ በአየር ኃይል ዋና አዘጋጅነት የተለያዩ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኖች፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመኾን የተለያዩ የአቪየሽን እና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትጥቆች ለዕይታ ቀርበዋል።

በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ በአየር ኃይሉ የተሰራችው እና ለበረራ ዝግጁ የተደረገችው “ፀሐይ ሁለት” አውሮፕላንም ለዕይታ ቀርባለች።

ኤግዚቢሽኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተው መጎብኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጥል ይልቅ በፍቅር ተሳስረን እንድንኖር የሚያስችሉን ታሪኮች ያሉን ሕዝቦች ነን” አፈ ጉባኤ መንግሥቱ ቤተ
Next articleየሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የአካል ጉዳተኞችን ምቾት ታሳቢ እንዲያደርጉ ተጠየቀ።