“እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጥል ይልቅ በፍቅር ተሳስረን እንድንኖር የሚያስችሉን ታሪኮች ያሉን ሕዝቦች ነን” አፈ ጉባኤ መንግሥቱ ቤተ

16

ደብረ ብርሃን: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አዘጋጅነት ነው እየተከበረ ያለው። በክብረ በዓሉ የከተማ አሥተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ መንግሥቱ ቤተ፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ የከተማ አሥተዳድሩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክርቤት አፈ ጉባኤ መንግሥቱ ቤተ “እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጥል ይልቅ በፍቅር ተሳስረን እንድንኖር የሚያስችሉን ታሪኮች ያሉን ሕዝቦች ነን” ብለዋል።

አፈ ጉባኤው ትላንት የነበረንን ሀገራዊ አንድነት እና ትስስር በማጠናከር ለነገ ሀገር ግንባታችን እንደ እርሾ መጠቀም ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰሜን ጎጃም ዞን የእርሻ ትራክተሮችን ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች አስረከበ።
Next articleየአየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው።