የሰሜን ጎጃም ዞን የእርሻ ትራክተሮችን ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች አስረከበ።

50

ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የእርሻ ትራክተሮችን ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች አስረክቧል።

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሣህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ እና የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የእርሻ ትራክተሮችን ለተጠቃሚዎች ከማስተላለፍ ባለፈ የበጋ መሥኖ ስንዴ ልማት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብርም ይካሄዳል።

የሰሜን ጎጃም ዞን ለዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ ከተመቹ የአማራ ክልል አካባቢዎች አንደኛው ነው። በክልሉ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግብርና ሥራዎችን ማከናወን ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ561 ቶን በላይ ዓሣ ተመርቷል።
Next article“እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጥል ይልቅ በፍቅር ተሳስረን እንድንኖር የሚያስችሉን ታሪኮች ያሉን ሕዝቦች ነን” አፈ ጉባኤ መንግሥቱ ቤተ